አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ በ10.15 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ለመገንባት ውል ተፈራረመ።
በዛሬው ዕለት በግብርና ሚኒስቴር የተደረገው ስምምነት በኢትዮጵያ የዶሮ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮግራም ስር የተፈረመ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የዶሮ ምርት አቅም ለማሳደግ እና በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጥራት ያለውን የምርት ግብዓት ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።
ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ የብድር ድጋፍ የሚገነባው ይህ ፕሮጀክት በዓመት 63 ሚሊዮን እንቁላል የማሳቀፍ አቅም ይኖረዋል፡፡
ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1C2eNkFKZz/
የዓለም የወተት ቀን በኢትዮጵያ መከበሩ በወተት እሴት ሰንሰለቱ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የዘርፉን እድገትና እድሎች ያሳየ አስፈላጊ መድረክ ሆኗል። በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ድጋፍ የኢትዮጵያ የወተት ምርት ከ7.1 ቢሊዮን ሊትር ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማደጉ የዘርፉን እመርታ ያሳያል። African Livestock Exhibition and Congress (ALEC) ይህን እድገት በማድነቅ በወተት ዘርፉ የእውቀት ልውውጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የገበያ ትስስር ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶችን ይደግፋል።
በወተት ልማት እሴት ሰንሰለት የተሰማሩ ተዋንያንን ያገናኘው የዓለም የወተት ቀን
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የዓለም የወተት ቀንን በድምቀት አክብሯል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢኒሼቲቩ የዝርያ ማሻሻያ፣ መኖ አቅርቦት እና የእንስሳት ጤናን በማሳደግ ብሎም ለባለድርሻ አካላት ንቅናቄ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል።
በ2014 ዓ.ም 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የነበረው የሀገሪቱ የወተት ምርት በ2018 ዓ.ም ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
መድረኩ የወተት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ ለመወያየት፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ተወካይ ናማኮሎ ኮቪች (ዶ/ር) ስለ ዓለም የወተት ቀን ስናስብ መጀመሪያ ወደ አእምሯችን ሊመጣ የሚገባው ስርዓተ-ምግብ መሆኑን ጠቁመው በህጻናት ላይ የሚስተዋለውን የመቀንጨር ችግር ለመከላከል ወተት ልማት ላይ በስፋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ (ዶ/ር) በበኩላቸው የወተት ምርትና ምርታማትን ለማሳደግ ከ500 በላይ አዳቃይ ባለሙያዎች የሰለጠኑ መሆኑንና እስካሁንም 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ላሞችን የማዳቀል ስራ በስኬት መከናወኑን ተናግረዋል።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አዝዝ አያሌው የወተት ዘርፍ ለግብርናው ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸው መደረኩ በባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ትስስር እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
ሙሉ ፅሑፍ ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1UjNAadNcm/
የእንስሳት ዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማዘመን ለዘርፉ ምርትና ምርታማነት እድገት ድሬዳዋ፣ መጋቢት 18/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የእንስሳት ዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማዘመን የሚያስችሉ መመሪያዎች በስፋት መዘጋጀትና በአግባቡ መተግበር ለዘርፉ ምርትና ምርታማነት እድገት ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡የእንስሳት ክትባት አቅርቦት፣ አያያዝ፣ ስርጭት እንዲሁም አጠቃቀም መመሪያና የዶሮ ስነ-ህይወት ደህንነት ረቂቅ መመሪያ ሰነዶች ላይ የፊደራል፣ የድሬደዋ መስተዳድር፣ የሶማሌ፣ የአፋርና የሀረሪ ክልሎች የዘርፉ ኃላፊዎችና ባላሙያዎች እንዲሁም የህግ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተወያይተዋል፡፡ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://www.facebook.com/share/1EgbCQkN92/
የወተት ሃብት ልማቱን በመፍጠርና መፍጠን መርህ መደገፍአዲስ አበባ፣ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (ግብርና ሚኒስቴር) እንደ ሀገር የወተት ሃብት ልማቱን ለማሳደግ በዝርያ ማሻሻል፣ በአያያዝ፣ በአመጋገብና ጤናን በማሻሻል የምርት ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ የወተት ሃብት ልማቱ ካለው ሰፊ ፀጋ አንጻር ለሀገር የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋፅኦ ለማሳደግ በዘርፉ ዋና ተዋንያን የሆኑት መንግስት፣ አገር አቀፍና አለም አቀፍ የምርምር ተቋማት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በጋራ መስራት ይገባቸዋል፡፡
ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1Fbr9mHkQb/
የስጋ ወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ የኤክስፖርት ቄራዎችን አቅም መገንባት!
(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
ከእንስሳት ሃብት ዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ በዘርፉ የሚታየውን ችግር መፍታት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘም የኤክስፖርት ቄራዎችን አቅም በማሳደግ ከስጋ ወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም በእንስሳት ሃብት ዘርፉ የስጋ ወጭ ንግድ የዕሴት ሰንሰለት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችል የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል።
ሙሉ ዜናውን ለማንበብ
https://web.facebook.com/share/p/14UzdMP6AS1/
የእንስሳት ምርት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች እየተዘረጉ ነው
(አዲስ አበባ፣ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
የእንስሳት ምርት ጥራትና ደህንነትን በዘላቂነት ለመጠበቅና የዘርፉን አሰራር ለማዘመን የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን እየዘረጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ገለጸ።
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የረቂቅ ደንቡን ይዘት በባለድርሻ አካላት ግብዓት ለማዳበር ያለመ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል።
ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://www.facebook.com/share/1E3czKt8fa/
የእንስሳት ኢንቨስመንት ግብይት ስትራቴጂን ለማርቀቅ እንዲሁም የእንስሳትና እንስሳት ውጤት ግብይት ረቂቅ አዋጅን ማዳበር የሚያስችል ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ዴስክ ኃላፊ አቶ ከድር ሉባንጎ መንግስት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና መመሪያዎችን በመቅረፅ ከእንስሳት ሀብቱ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የእንስሳትና እንስሳት ውጤት ግብይት ረቂቅ ስትራቴጂን እና አዋጅን ለአብነት የጠቀሱት ዴስክ ኃላፊው፣ ረቂቆቹ ፀድቀው ወደ ትግበራ ሲገቡ በእንስሳትና የእንስሳት ውጤት ግብይት ሂደት የምርት ጥራትን የሚያጓድሉ አሰራሮችን ያስቀራሉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከ70 ሚሊየን በላይ የዳልጋ ከብት ያላት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም አላገኘችም፡፡
የመኖ አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረት፣ የሀገር በቀል ዝሪያዎች ምርታማነታቸው አነስተኛ መሆን እንዲሁም በቂ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽ አለመሆን እንደ ተግዳሮት ይጠቀሳሉ፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ ስኬታማ የስድስት ወር አፈጻጸም እንዳስመዘገበች የግብርና ባለስልጣን አስታውቋል።
የስጋ ምርቷን ወደ ጎረቤት ሀገራት እና መካከለኛው ምስራቅ ብቻ ትልክ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን የሩቅ ምስራቅ ሀገራትን መድረስ እንደቻለች ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ቻይና እና ሞንጎሊያ ድረስ የተቀቀለ ስጋ መላክ መጀመሯን የግብርና ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለፈው ስድስት ወር ወደ ውጭ የተላከው የቁም እንሰሳት በ2016 ዓ.ም ሙሉ ዓመት ከተላከው የ100 ሺህ ብልጫ ያለው ሲሆን በገቢ ረገድ የ10 ሚሊዮን ዶላር ልዩነት እንዳለው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
Addis Ababa September 23/2024 (ENA) Ethiopia launched its first livestock export to Djibouti by rail, the CEO of Ethio-Djibouti Railways, Takele Uma disclosed today. “Today, we are launching our first livestock export from ADAMA to Djibouti by rail,” the CEO said on social media. This approach will maximize the use of our open wagons, which were previously used only for imports, Takele pointed out. According to him, the beginning of railways transport will also boost export meat quality by minimizing transport stress on animals, showcasing Ethiopia's commitment to efficient and sustainable trade. The move demonstrates Ethiopia’s dedication to enhancing capital flows across borders, Takele added.