NEWS

Latest News 

የዓለም የወተት ቀን

የዓለም የወተት ቀን

የዓለም የወተት ቀን በኢትዮጵያ መከበሩ በወተት እሴት ሰንሰለቱ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የዘርፉን እድገትና እድሎች ያሳየ አስፈላጊ መድረክ ሆኗል። በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ድጋፍ የኢትዮጵያ የወተት ምርት ከ7.1 ቢሊዮን ሊትር ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማደጉ የዘርፉን እመርታ ያሳያል። African Livestock Exhibition and Congress (ALEC) ይህን እድገት በማድነቅ በወተት ዘርፉ የእውቀት ልውውጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የገበያ ትስስር ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶችን ይደግፋል።

በወተት ልማት እሴት ሰንሰለት የተሰማሩ ተዋንያንን ያገናኘው የዓለም የወተት ቀን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የዓለም የወተት ቀንን በድምቀት አክብሯል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ የዝርያ ማሻሻያ፣ መኖ አቅርቦት እና የእንስሳት ጤናን በማሳደግ ብሎም ለባለድርሻ አካላት ንቅናቄ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል።

በ2014 ዓ.ም 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የነበረው የሀገሪቱ የወተት ምርት በ2018 ዓ.ም ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

መድረኩ የወተት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ ለመወያየት፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ተወካይ ናማኮሎ ኮቪች (ዶ/ር) ስለ ዓለም የወተት ቀን ስናስብ መጀመሪያ ወደ አእምሯችን ሊመጣ የሚገባው ስርዓተ-ምግብ መሆኑን ጠቁመው በህጻናት ላይ የሚስተዋለውን የመቀንጨር ችግር ለመከላከል ወተት ልማት ላይ በስፋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ (ዶ/ር) በበኩላቸው የወተት ምርትና ምርታማትን ለማሳደግ ከ500 በላይ አዳቃይ ባለሙያዎች የሰለጠኑ መሆኑንና እስካሁንም 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ላሞችን የማዳቀል ስራ በስኬት መከናወኑን ተናግረዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አዝዝ አያሌው የወተት ዘርፍ ለግብርናው ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸው መደረኩ በባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ትስስር እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

ሙሉ ፅሑፍ ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1UjNAadNcm/

More

የእንስሳት ዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማዘመን ለዘርፉ ምርትና ምርታማነት

የእንስሳት ዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማዘመን ለዘርፉ ምርትና ምርታማነት እድገት ድሬዳዋ፣ መጋቢት 18/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የእንስሳት ዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማዘመን የሚያስችሉ መመሪያዎች በስፋት መዘጋጀትና በአግባቡ መተግበር ለዘርፉ ምርትና ምርታማነት እድገት ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡የእንስሳት ክትባት አቅርቦት፣ አያያዝ፣ ስርጭት እንዲሁም አጠቃቀም መመሪያና የዶሮ ስነ-ህይወት ደህንነት ረቂቅ መመሪያ ሰነዶች ላይ የፊደራል፣ የድሬደዋ መስተዳድር፣ የሶማሌ፣ የአፋርና የሀረሪ ክልሎች የዘርፉ ኃላፊዎችና ባላሙያዎች እንዲሁም የህግ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተወያይተዋል፡፡ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://www.facebook.com/share/1EgbCQkN92/

More

የወተት ሃብት ልማቱን በመፍጠርና መፍጠን መርህ

የወተት ሃብት ልማቱን በመፍጠርና መፍጠን መርህ መደገፍአዲስ አበባ፣ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (ግብርና ሚኒስቴር) እንደ ሀገር የወተት ሃብት ልማቱን ለማሳደግ በዝርያ ማሻሻል፣ በአያያዝ፣ በአመጋገብና ጤናን በማሻሻል የምርት ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ የወተት ሃብት ልማቱ ካለው ሰፊ ፀጋ አንጻር ለሀገር የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋፅኦ ለማሳደግ በዘርፉ ዋና ተዋንያን የሆኑት መንግስት፣ አገር አቀፍና አለም አቀፍ የምርምር ተቋማት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በጋራ መስራት ይገባቸዋል፡፡

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1Fbr9mHkQb/

More

የስጋ ወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ የኤክስፖርት ቄራዎችን አቅም መገንባት!

የስጋ ወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ የኤክስፖርት ቄራዎችን አቅም መገንባት!

(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

ከእንስሳት ሃብት ዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ በዘርፉ የሚታየውን ችግር መፍታት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘም የኤክስፖርት ቄራዎችን አቅም በማሳደግ ከስጋ ወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም በእንስሳት ሃብት ዘርፉ የስጋ ወጭ ንግድ የዕሴት ሰንሰለት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችል የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል።

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ
https://web.facebook.com/share/p/14UzdMP6AS1/

More

የእንስሳት ምርት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች እየተዘረጉ ነው

የእንስሳት ምርት ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች እየተዘረጉ ነው

(አዲስ አበባ፣ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

የእንስሳት ምርት ጥራትና ደህንነትን በዘላቂነት ለመጠበቅና የዘርፉን አሰራር ለማዘመን የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን እየዘረጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ገለጸ።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የረቂቅ ደንቡን ይዘት በባለድርሻ አካላት ግብዓት ለማዳበር ያለመ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል።

ሙሉ ዜናውን ለማንበብ https://www.facebook.com/share/1E3czKt8fa/

More
የእንስሳት ኢንቨስመንት ግብይት ስትራቴጂን ለማርቀቅ እንዲሁም የእንስሳትና እንስሳት ውጤት ግብይት ረቂቅ አዋጅን ማዳበር የሚያስችል ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ዴስክ ኃላፊ አቶ ከድር ሉባንጎ መንግስት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና መመሪያዎችን በመቅረፅ ከእንስሳት ሀብቱ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የእንስሳትና እንስሳት ውጤት ግብይት ረቂቅ ስትራቴጂን እና አዋጅን ለአብነት የጠቀሱት ዴስክ ኃላፊው፣ ረቂቆቹ ፀድቀው ወደ ትግበራ ሲገቡ በእንስሳትና የእንስሳት ውጤት ግብይት ሂደት የምርት ጥራትን የሚያጓድሉ አሰራሮችን ያስቀራሉ ብለዋል፡፡

የህግ ማዕቀፎች የእንስሳት ምርት ግብይት ስርዓትን ያሳልጣሉ

የእንስሳት ኢንቨስመንት ግብይት ስትራቴጂን ለማርቀቅ እንዲሁም የእንስሳትና እንስሳት ውጤት ግብይት ረቂቅ አዋጅን ማዳበር የሚያስችል ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ኢንቨስትመንትና ምርት ግብይት ዴስክ ኃላፊ አቶ ከድር ሉባንጎ መንግስት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን እና መመሪያዎችን በመቅረፅ ከእንስሳት ሀብቱ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የእንስሳትና እንስሳት ውጤት ግብይት ረቂቅ ስትራቴጂን እና አዋጅን ለአብነት የጠቀሱት ዴስክ ኃላፊው፣ ረቂቆቹ ፀድቀው ወደ ትግበራ ሲገቡ በእንስሳትና የእንስሳት ውጤት ግብይት ሂደት የምርት ጥራትን የሚያጓድሉ አሰራሮችን ያስቀራሉ ብለዋል፡፡

More
1 2 3 4 5

Nothing More to load

No more pages to load

Organizer

Partner Events

Diamond Sponsor

Institutional Partners

UNIDO

Media Partners

Member of

Registration Partner

Official Hotel Partners

Ramada

Official Airline Partner

bullhornclock
linkedin facebook pinterest youtube rss twitter instagram facebook-blank rss-blank linkedin-blank pinterest youtube twitter instagram