የዓለም የወተት ቀን በኢትዮጵያ መከበሩ በወተት እሴት ሰንሰለቱ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የዘርፉን እድገትና እድሎች ያሳየ አስፈላጊ መድረክ ሆኗል። በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ድጋፍ የኢትዮጵያ የወተት ምርት ከ7.1 ቢሊዮን ሊትር ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማደጉ የዘርፉን እመርታ ያሳያል። African Livestock Exhibition and Congress (ALEC) ይህን እድገት በማድነቅ በወተት ዘርፉ የእውቀት ልውውጥ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የገበያ ትስስር ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶችን ይደግፋል።

በወተት ልማት እሴት ሰንሰለት የተሰማሩ ተዋንያንን ያገናኘው የዓለም የወተት ቀን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የዓለም የወተት ቀንን በድምቀት አክብሯል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ የዝርያ ማሻሻያ፣ መኖ አቅርቦት እና የእንስሳት ጤናን በማሳደግ ብሎም ለባለድርሻ አካላት ንቅናቄ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል።

በ2014 ዓ.ም 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የነበረው የሀገሪቱ የወተት ምርት በ2018 ዓ.ም ወደ 16 ቢሊዮን ሊትር ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

መድረኩ የወተት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ ለመወያየት፣ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረውም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ተወካይ ናማኮሎ ኮቪች (ዶ/ር) ስለ ዓለም የወተት ቀን ስናስብ መጀመሪያ ወደ አእምሯችን ሊመጣ የሚገባው ስርዓተ-ምግብ መሆኑን ጠቁመው በህጻናት ላይ የሚስተዋለውን የመቀንጨር ችግር ለመከላከል ወተት ልማት ላይ በስፋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስራት ጤራ (ዶ/ር) በበኩላቸው የወተት ምርትና ምርታማትን ለማሳደግ ከ500 በላይ አዳቃይ ባለሙያዎች የሰለጠኑ መሆኑንና እስካሁንም 4 ነጥብ 9 ሚሊዮን ላሞችን የማዳቀል ስራ በስኬት መከናወኑን ተናግረዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አዝዝ አያሌው የወተት ዘርፍ ለግብርናው ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸው መደረኩ በባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ ትስስር እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

ሙሉ ፅሑፍ ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/1UjNAadNcm/

Organizer

Partner Events

Diamond Sponsor

Institutional Partners

UNIDO

Media Partners

Member of

Registration Partner

Official Hotel Partners

Ramada

Official Airline Partner

bullhornclock
linkedin facebook pinterest youtube rss twitter instagram facebook-blank rss-blank linkedin-blank pinterest youtube twitter instagram